በቪክቶሪያ ህግ መሰረት፤ ስለ መንግሥታዊ የአእምሮ ጤና ጥበቃ አገልግሎት አስመልክቶ ለመናገርና ቅሬታ የማሰማት መብት አለዎት።

የአእምሮ ጤና ቅሬታ ሰሚ ኮሚሽነር/Mental Health Complaints Commissioner (MHCC) በቪክቶሪያ ውስጥ ስላሉ መንግሥታዊ የአእምሮ ጤና ጥበቃ አገልግሎቶች ለሚቀርቡ ቅሬታዎች ይደራደራል። ይህም በህዝባዊ ገንዘብ እርዳታ ለተመሰረቱ የአእምሮ ጤና ጥበቃ ማህበረሰብ ድጋፍ አገልግሎቶች እና በ NDIS (በብሔራዊ አካለ ጉዳተኛ ኢንሹራንስ/ዋስትና ፕሮግራም) ገንዘብ እርዳታ የሚያገኝ የአእምሮ ጤና ጥበቃ ማህበረሰብ ድጋፍ አገልግሎቶችን ያጠቃልላል።

ከአገልግሎቱ ጋር በተዛመደ ስላጋጠመዎት ችግር ቅሬታ እንዲያቀርቡ ልንረዳዎት እንችላለን፤ ይህም ስለሚቀርብልዎ አገልግሎት፤ ህክምናና እንክብካቤን ያካትታል። እርስዎ ስላለብዎት ስጋት በቀጥታ ለአገልግሎት ሰጪው ቅሬታዎን ማቅረብ እንዲችሉ እንረዳዎታለን፡ ከእርስዎ እና ከአገልግሎት ሰጪው ጋራ በመስራት ያለብዎትን ስጋት እንዲፈቱ ልንረዳዎ እንችላለን፡ እንዲሁም እኛ መርዳት ካልቻልን ሌላ አማራጮችን እንወያያለን።

ማን ነው ቅሬታ ሊያሰማ የሚችለው?

የመንግሥት አእምሮ ጤና ጥበቃ አገልግሎቶችን የሚያገኙ ሰዎች፤ ቤተሰቦች፤ ተንከባካቢዎች፤ ድጋፍ ሰጪዎች፤ የአእምሮ ጤና ጥበቃ ሠራተኞችና ጓደኞች – ማንኛውም ሰው ከመንግሥት የአእምሮ ጤና ጥበቃ አገልግሎት ጋር በተዛመደ ስለሌላው ተጠቃሚ እውነተኛ ስጋት ካለው ቅሬታ ማቅረብ ይችላል።

እኛን መጠቀም ይቻላል

በማንኛውም ቋንቋ በአስተርጓሚ በኩል የሚቀርቡ ቅሬታዎችን ተቀብለን እናዳምጣለን። አስፈላጊ ከሆነ አስተርጓሚ ያለክፍያ በነጻ እናዘጋጅልዎታለን።

እኛን ያነጋግሩ

ስላለዎት ስጋቶች ለማነጋገር ወይም ቅሬታ ለማሰማት:

  • በስልክ 1800 246 054 (ከቤት ስልክ ከሆነያለክፍያ በነጻ ጥሪ) ወይም 03 9032 3328 መደወል
  • ኢሜል help@mhcc.vic.gov.au
  • ፋክስ 03 9949 1506
  • በአካል ለመጎብኘት አድራሻ፡ Level 26, 570 Bourke Street, Melbourne Victoria.

ለበረጠ መረጃ

ቅሬታ ስለማቅረብ የመረጃ ጽሁፍ ወረቀት